Find Posts By Topic

የንግድ ሥራዎን ይዞታ ማግኘት

Finding Your Business Occupancy

የአገረ ገዢው 2ኛ ዙር መመሪያ ለደህንነቱን የጠበቀ የመልሶ መክፈት እቅድ

Bakery business owners with a pie.ኪንግ ካውንቲ ከዋሽንግተን ግዛት የጤና ፀሀፊ ወደ አገረ ገዢው 2ኛ ዙር ደህንነቱን የጠበቀ መልሶ መክፈት እቅድ እንዲዘዋወር ፈቃድ አግኝቷል፣ ይህ አንዳንድ ንግዶች እና እንቅስቃሴዎች ስራ እንዲጨምሩ መፍቀድ እንዲሁም በቦታው ውስጥ ያሉትን ሰዎች ቁጥር መገደብ፣ እንደገና በሚከፈተው እቅድ ውስጥ “ይዞታ” ተብሎ ተጠርቷል፡፡ የቴክኒክ ቃሉ “የይዞታ ጭነት” ነው። የተፈቀደውን 2ኛ ዙር ዕቅድ እዚህ እና የአገረ ገዢው የመልሶ መክፈት መመሪያእዚህይመልከቱ። 

በመልሶ መክፈት ዕቅድ ስር ላለው ቦታዎ የይዞታውን ጭነት ለማግኘት የሚረዱ ዘዴዎች፡-

  1. የተለጠፈ ይዞታ። በንግድዎ ውስጥ የተለጠፈ የይዞታ ገደብ ካለዎት፣ የተቀነሰ የይዞታ ጭነትዎን ሲያሰሉ እንደ መነሻ ይጠቀሙበት፡፡ የይዞታ ገደብ ምልክቶች በስብሰባዎች አዳራሾች ውስጥ ብዙ ምግብ ቤቶችን እና ባሮችን ጨምሮ 50 ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች በሚኖሩበት ቦታ ላይ ተለጥፈዋል፡፡ መልሶ በሚከፈተው ዕቅድ ስር የተፈቀደ የነዋሪነት ይዞታዎን ለማግኘት፣ የተለጠፈ ጭነትዎን በተቀነሰ የይዞታ ደረጃ (ከዚህ በታች ባሉት አምዶች D ያባዙ እና ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የአገረ ገዢውን የንግድ እንቅስቃሴ መመሪያዎች ይመልከቱ።
  2. የቅርብ ጊዜ የፍቃድ ቁሳቁሶች። በቅርብ ጊዜ በእርስዎ ቦታ ውስጥ ለተከራዮች ማሻሻያ ፈቃድ ከተቀበሉ፣ የቦታዎ ትክክለኛ የይዞታ ጭነት በተረጋገጠ ፈቃድ ዕቅዶች ላይ ሊገኝ ይችላል፡፡ የመጨረሻውን የግንባታ ፈቃድ ዕቅዶች ቅጂ አሁንም ካለዎት፣ የይፋ ቁጥሩን ለማግኘት ይህ በጣም ቀላሉ እና ፈጣኑ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ወደ Department of Construction & Inspections (SDCI፣ የግንባታ እና የቁጥጥር ክፍል) የፕሮጀክት ፖርታል በመግባት የፀደቁ ዕቅዶችን ወይም ፈቃዱን የንድፍ ባለሙያውን በማነጋገር ማግኘት ይችሉ ይሆናል።
  3. ካሬ ጫማ ላይ የተመሠረተ ግምት። SDCI መደበኛውን የተያዘው ይዞታዎን ለመገመት እና በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጭ ቦታዎች ላይ በመልሶ የመክፈት እቅዱ ስር ምን ያህል ሰዎች ማስገባት እንደተፈቀደ ለመገመት እንዲረዳዎት ከዚህ በታች ያለውን ማትሪክስ አዘጋጅቷል፡፡ አምድ B እና C የነባር የይዞታ ጭነትዎን ለመገመት መጠቀም ከሚፈቀደው ይዞታ ቁጥር በታች ሊሆን ይችላል ነገር ግን አሁን ያለዎትን የይዞታ ጭነት ካላወቁ አማራጭ ነው።
  አሁን ያለዎትን የነዋሪ ጭነት መገመት የመልሶ መክፈቻ ይዞታዎን ማግኘት
አምድ A አምድ B አምድ C አምድ D
የንግድ ዓይነት

(እና ወደ WA ግዛት

የንግድ እንቅስቃሴ መመሪያዎች አገናኝ)

የሚለኩ አካባቢዎች

ግምት ሲሰላ

መደበኛ

የይዞታ ጭነት አካፋይ

(ካሬ ጫማ በአንድ ሰው)

ዙር 2

የተቀነሰ የይዞታ ደረጃ

ሬስቶራንቶች/ባሮች (መመገቢያ)

– ከቤት ውጭ የመመገቢያ ቦታዎች

የደንበኞች መመገቢያ ቦታዎች 15 50%*
– የቤት ውስጥ የመመገቢያ ቦታዎች የደንበኞች መመገቢያ ቦታዎች 15 50%*
– የባር መቀመጫ የደንበኞች መመገቢያ ቦታዎች 15 አልተፈቀደም
ችርቻሮ (በመደብር ውስጥ) የሽያጭ ወለሎች 60 30%
የአካል ብቃት ስቱዲዮዎች (የቤት ውስጥ) የሰውነት እንቅስቃሴ ቦታዎች 50 30%*
የሐይማኖት እና የእምነት ድርጅቶች (ቤት ውስጥ) የአምልኮ ቦታዎች 15 25%
የግል አገልግሎቶች ሁሉም የቤት ውስጥ ቦታዎች 100 50%
የእንስሣት ማጠቢያ/ማስተካከያ ሁሉም የቤት ውስጥ ቦታዎች 100 50%
የባለሙያ አገልግሎቶች ሁሉም የቤት ውስጥ ቦታዎች 100 50%
Real Estate ሁሉም የቤት ውስጥ ቦታዎች 100 50%

 

*ሌሎች ገደቦች እንዲሁ የተፈቀደላቸውን ሰዎች ብዛት ሊገድቡ ይችላሉ። የ King County ን የተፈቀደ/የጸደቀ 2ኛ ዙር እቅድን እና የ አገረ ገዢውን 2ኛ ዙር የንግድ እንቅስቃሴ መምሪያዎች ለበለጠ መረጃ ይመልከቱ።

የይዞታ ጭነትዎን መገመት:-

    1. በአምድ B ውስጥ የተመዘገበውን የወለል ስፋት መጠን ይፈልጉ። በኪራይ ስምምነትዎ ፣ በየትኛውም ወለል ዕቅዶችዎ፣ ወይም ለቦታዎ የይዞታ የምስክር ወረቀት ለማግኘት የቦታዎን ካሬ ስፋት ያገኙ ይሆናል፡፡ በማንኛውም ሰነድ ውስጥ የቦታዎን ጫማ ካሬ (ካ.ጫ.) መወሰን ካልቻሉ የሚመለከታቸው ቦታዎችን ርዝመት እና ስፋት (በጫማ) መለካት ይችላሉ። አንድን ቦታ ካ.ጫ. ለማግኘት የተለካውን ርዝመት እና ስፋት አንድ ላይ ያባዙ።
    2. የቦታዎን ስፋት በመደበኛ የይዞታ ጭነት አካፋይ (አምድ C) ያካፍሉት። ወደ ቅርቡ ሙሉ ቁጥር ማጠጋጋት ይችላሉ።

የሬስቶራንት ምሳሌ፡- 1,000 ካ.ጫ. የመመገቢያ ቦታ / 15 ካ.ጫ. በአንድ ሰው = እስከ 67 ሰዎች

የችርቻሮ መደብር ምሳሌ፡-1,000 ካ.ጫ. የሽያጭ ወለል / 60 ካ.ጫ. በአንድ ሰው = እስከ 17 ሰዎች

በመልሶ መክፈቻው እቅድ መሠረት የተፈቀደልዎትን የተቀነሰ የይዞታ ጭነትዎን መፈለግ፡-

    1.  መደበኛውን የይዞታ ጭነትዎን በ 2ኛው ዙር በተቀነሰ የነዋሪነት ደረጃ (በአምድ D) ያባዙ።

የሬስቶራንት ምሳሌ፡- 67 ሰዎች x 0.50 = እስከ 34 ሰዎች ተፈቅዷል

የችርቻሮ መደብር ምሳሌ፡-17 ሰዎች x 0.30 = እስከ 5 ሰዎች ተፈቅዷል

    1. ለበለጠ ምሪት እና ለንግድዎ የተፈቀደ የሰዎች ቁጥር ወሰን የ King County ን የተፈቀደ/የጸደቀ 2ኛ ዙር እቅድን እና የ አገረ ገዢውን 2ኛ ዙር የንግድ እንቅስቃሴ መምሪያዎች ይመልከቱ።
  1. ታሪካዊ ፈቃድ ምርምር። SDCI ታሪካዊ ፈቃድ መስጫ ሰነዶችን ለመመርመር ሊረዳዎት ይችል ይሆናል፣ ሆኖም የፍቃድ መዝገቦችን ለመከታተል ጊዜ ይወስዳል፣ እና ደግሞ የቆዩ የታሪክ መዛግብት ላይገኙ ይችላሉ። SDCI ከላይ ያሉትን ዘዴዎች 1-3 እንዲጠቀሙ ይመክራል።

 

የበለጠ መረጃ

በሲያትል ውስጥ በዙር 2 ስር ስለመስራት ያሉ ጥያቄዎች? በ 206-684-8090 ለ Office of Economic Development (ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት) ይደውሉ። የቋንቋ እርዳታ ማግኘት ይቻላል። ስለመደበኛ የይዞታ ጭነትዎ ያሉ ጥያቄዎች? በ http://web6.seattle.gov/dpd/LUQnA/?Type=2 በመስመር ላይ ያስገቧቸው